tag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post3980374973892217468..comments2024-01-01T19:56:24.236-08:00Comments on The Q: የባለፀጋዋን አገር ዜጋ፤ አቶ ድህነትን እናስተዋውቅዎBefeQadu Z Hailuhttp://www.blogger.com/profile/10090745447582888476noreply@blogger.comBlogger2125tag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-7400397977627868992012-07-05T07:53:43.342-07:002012-07-05T07:53:43.342-07:00ከመዘግነን አልፎ የሚያስደነግጥ ነገር ነው! ብሎም የሚያሳፍር እና ልብ የሚሰብር...ከመዘግነን አልፎ የሚያስደነግጥ ነገር ነው! ብሎም የሚያሳፍር እና ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ግን መፍትሄ የሌለው ችግር የለም፡ የተማረው የሰው ሃይል ቁጥር በዝቶ ካለው ፍላጎት ጋር ካልተመጣጠነ ትልቁ ችግር ይሄ ነው፡፡ እውነት ነው ብዙ በዲግሪ እና በማስተርስ የተመረቁ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ምሁራን በየጊዜው ይመረቃሉ ነገር ግን እነዚህ ምሁራን የሚቀበል መስሪያ ቤት እና ድርጅቶች በቂ አይደሉም፡፡ በቂ እንዲሆኑ አልተፈለገም ይሁን ለምን አልኖሩንም የሚለው ቀጣይ ዋና ችግር ነው! እንደው ከጀመርኩት አይቀር የግድ አንድ ሰው ተመረቀና ስራ ፈልጎ መቀጠር አለበት በሚለው ነጥብም ብዙ አልስማማም፡፡ እንዲያውም የስራ ፈጣሪ ነው መሆን ያለበት በሚለው የበለጠ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን በአጠቃላይ የትምህርት ፖሊሲያችን ስራ ፈጣሪነትን የሚያበረታታ እና የሚያሳድግ አይደለም እዚህ ጋር መስተካከያዎች ቢደረጉበት የተማረው ምሁር በትንሽ ነገር ተነስቶ ሀገር እስከመለወጥ ይደርሳል፣ ለሌላውም ይተርፋል፡፡ <br /> ሌላው ነጥብ ደግሞ አዳዲስ የሚመሰረቱ ማንኛውንም አነስተኛ እና ጥቃቅን ድርጅቶችን በደምብ እራሳቸውን ችለው እስኪቋቋሙ ድረስ ማበረታታት እና መደገፍ ያስፈልጋል፡፡ ቀደም ባለው ስርአት እስከ 6 ወር አንድ አመት ድረስ ታክስ አይከፈልም ነበር አሁን ስርዓቱ ተቀይሯል፡ አይደለም ድርጅቱ እስኪቋቋም ቀርቶ ያለውንም ማፈናፈን ያልቻለ አሰራር ነው የተመሰረተው ነገር ግን ማስተካከያ ቢደረግበት የተሻለ ውጤት ያመጣል፣ አልፎ ተርፎም ቅድም ከላይ የተነሱትን የምሁራን ጉዳይ በቂ መልስ ይሰጣል፡፡ እርግጠኛ ያልሆንኩት ግን የሰማሁት፡ የቻይና መንግስስት አዲስ ለሚመሰረቱ ትናንሽ ድርጅቶች በተቻለው መጠን ያግዛል፡፡ አንድ ቻይናዊ ድርጅት መክፈት ቢፈልግ የሚያስፈልገውን ካፒታል እና አትራፊ ነው አይደለም የሚለው ታይቶ መንግስት ጣልቃ ገብቶ በጋራ ባለቤትነት ወይም በፐርሰንት ተካፍሎ ያስተዳድራል፡፡ በዚህ ባለቤቱም ተጠቀመ፣ መንግስት ተጠቀመ፣ ሃገር ተጠቀመ ማለት ነው! አሁን ግን በትክክል መንግስት ከቅሚያ ያልተናነሰ ስራ ነው እየተሰራ ያለው፡፡ <br />ምነው ከነቻይናና ህንድ እንደዚህ እንደዚህ አይነት ሃሳቦችን ከመውሰድ ነጻነትን ማፈኛ መሳሪያ መግዛት በለጠባቸው???Anonymoushttps://www.blogger.com/profile/11464255335057379937noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-86441844733887533742012-07-05T05:58:24.555-07:002012-07-05T05:58:24.555-07:00ዝግንን የሚል ነገር ነው፡፡ ምን ይሻለን ይሆንዝግንን የሚል ነገር ነው፡፡ ምን ይሻለን ይሆንቤተሥላሴ ናኦድ https://www.blogger.com/profile/00986480811642164804noreply@blogger.com