tag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post5570942936571711294..comments2024-01-01T19:56:24.236-08:00Comments on The Q: የፈረንጅ አምልኮ በኢትዮጵያBefeQadu Z Hailuhttp://www.blogger.com/profile/10090745447582888476noreply@blogger.comBlogger4125tag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-60414973510235409392012-07-12T23:01:15.383-07:002012-07-12T23:01:15.383-07:00Naod is right. ፈረንጅ የሚለው ቃል French ከሚለው የመጣ ነው::Naod is right. ፈረንጅ የሚለው ቃል French ከሚለው የመጣ ነው::Bibihttps://www.blogger.com/profile/16077816865065628431noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-54149523474148699112012-04-05T22:20:31.702-07:002012-04-05T22:20:31.702-07:00ከገመቱ ምሁራዊ ግምት መገመት ነው አለበለዚያ የሰሙትን ብቻ መናገር ቀደም ብሎ ...ከገመቱ ምሁራዊ ግምት መገመት ነው አለበለዚያ የሰሙትን ብቻ መናገር ቀደም ብሎ የፈረንሳይ የእንግሊዝ ሰዎች ባማካሪነትና በሙያ ይገቡ ስለነበረ ከፍሬንች ፈረንጅ ተባለ ነበር በሰፊው የሚታወቀው ዛሬ ታዲያ foreign የሚል ቃል የሚያውቅ ተወለደና ጋለል ብሎ በኩራት ታሪክ ሊፈጠርልን ኤጭ።Anonymousnoreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-80457336495734516642012-01-22T00:26:45.205-08:002012-01-22T00:26:45.205-08:00ለነገሩ ፈረንጅ የሚለው ቃል÷ French ከሚለው ቃል ጋር በድምጽ በጣም እንደሚ...ለነገሩ ፈረንጅ የሚለው ቃል÷ French ከሚለው ቃል ጋር በድምጽ በጣም እንደሚዛመዱ አስተውያለሁ፡፡ ይሄ ጽሁፍ ethiopianreview.com ላይ ተለጥፎ አይቼዋለሁ፤ እዚያም አንድ ሰው ይህንኑ በአስተያየቱ ጠቁሟል፡፡ እኔም በጽሁፉ ላይ መላምቴን ነው ያስቀመጥኩት፡፡ <br />እንዳልከው ፈረንጅን የሚያመልኩ ብዙ ሃገራት (ወይም ፈረንጆች) ሊኖሩ ይችላሉ፤ ቢሆንም የእኛ አገር የባዕድ (የፈረንጅ አምልኮ) ግን - ያው ስለውጪው ዓለም (ስለፈረንጆች) ማወቅ ከጀመርንበት ዘመን ይጀምራል ባይ ነኝ፡፡ በርግጥ ከዚያ በፊትም በንግድ እናውቃቸው ነበር፡፡ ቢሆንም በበላይነት ዘመን የምታውቃቸውን ሰዎች ከማምለክ (ወይም ለመምሰል ከመሞከር ይልቅ)፣ አምላክን ይዘው የአምላክ ቤተሰብ ሁነው የመጡ ሰዎችን ለመምሰል መሞከር ይቀላል፡፡ ለዚያ ነው ክርስትና ላይ ጣቴን የቀሰርኩት፡፡<br />በነገርህ ላይ÷ ethiopianreview ላይም ብዙዎቹ አስተያየት የሰጡት ይቺን የክርስትናን ወደኢትዮጵያ መግባት ተከትሎ የመጣ የባዕድ አምልኮ ‹‹የምታብጠለጥል›› ሁለት አንቀጽ መሠረት አድርገው እንጂ በጥቅል የጽሁፉ ይዘት ውስጥ ለማስተላለፍ የሞከርኩት መልዕክት ላይ አይደለም፡፡ አንዴ፤ ገጠርነታቸው ካልለቀቃቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሄጄ ያየሁትን ‹‹ድሮ›› (አንተ በአንድ ጽሁፍህ እንደጠቀስከው በ‹ታይም ሜሽን› የተመለስኩ ነበር የመሰለኝ፤) እናም ያንን ‹‹ድሮ›› ተከትለን ብንመጣ የት እንደርስ እንደነበር (ወይም ማን እንሆን እንደነበር) የምጽፍ ይመስለኛል፡፡BefeQadu Z Hailuhttps://www.blogger.com/profile/10090745447582888476noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-29885089615999366862012-01-21T21:18:51.342-08:002012-01-21T21:18:51.342-08:00ፈረንጅ የሚለው ቃል French ከሚለው የመጣ ይመስለኝ ነበር፡፡
ጽሑፉ ደስ ይላ...ፈረንጅ የሚለው ቃል French ከሚለው የመጣ ይመስለኝ ነበር፡፡<br />ጽሑፉ ደስ ይላል፡፡ ፈረንጅን ስንከተል መኖራችን እኔንም ሆነ ሌሎችን ሲከነክን የሚኖር ጉዳይ ነው፡፡ መድሀኒቱ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ መድሀኒቱን ለማወቅ፤ ችግሩን ማወቅ አንድ እርምጃ ነው ብዬ በማሰብ አንተ ግን እንደ ችግሩ ምክንያት ያስቀመጥከው ነገር ገመገምኩት፡፡…እና ትንተናህ ብዙ አላሳመነኝም፡፡ <br />ፈረንጅ ማምለክ የኢትዬጵያ ብቻ ችግር፤ መነሻውም ክርስትና አድርገህ ማስቀመጥህ አኒክዶታል ወይም የተጋነነ ጄኔራላይዜሽን መሰለኝ፡፡ ለምን ብትለኝ ‹‹ፈረንጅን የሚያመልኩ›› ብዙ ሀገሮች እና ሕዝቦች በዙሪያችን አሉና፡፡ብዙዎቹ ክርስቲያን አይደሉም፡፡ ነገሩ የመላው አፍሪካ..የመላው አዳጊ እና ታዳጊ ሀገር ችግር ነው፡፡ ሕንድና ቻይና፤ ዓረቡ እና ላቲን አሜሪካው ፈረንጅ ለመምሰል ሲሽቀዳደሙ አላስተዋልክም፡፡ ከፈረንጆችም ውስጥ ደንበኛ ፈረንጅ ለመሆን የሚደረግ ጥረት አለ፡፡ ባለ ወርቃማ ጸጉር መሆን፤ ረጅም እና ፈርጣማ መሆን፤ ባለ ሰማያዊ ዓይን መሆን…ወዘተ፡፡ ጸጉሯን ብሎንድ ለማድረግ ሃይላት የማትቀባ ሴት ፈረንጅ ያለች እንዳትመስልህ፡፡ ነገሩ በእኛ ብሶ ታየ እንጂ፤ በሁሉም ቤት ያለ ግሎባል ችግር ነው ባይ ነኝ፡፡ መፍትሔውም ከእኛ በላይ የሆነ ግሎባል ይመስለኛል፡፡ቤተሥላሴ ናኦድ https://www.blogger.com/profile/00986480811642164804noreply@blogger.com