tag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post5537013221403231525..comments2024-01-01T19:56:24.236-08:00Comments on The Q: የተዋሐደን ፆተኝነትBefeQadu Z Hailuhttp://www.blogger.com/profile/10090745447582888476noreply@blogger.comBlogger2125tag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-38534586631926902042017-08-27T05:33:09.381-07:002017-08-27T05:33:09.381-07:00የተከበርሽ አኖኒመስ፣
ረዘም ያለ ጊዜ ወስደሽ አስተያየት በመስጠትሽ ተደስቻለሁ።...የተከበርሽ አኖኒመስ፣
ረዘም ያለ ጊዜ ወስደሽ አስተያየት በመስጠትሽ ተደስቻለሁ። ሆኖም አስተያየቶችሽ ውኃ የሚያነሱ ሆነው እንዳላገኘኋቸው አልሸሽግሽም።

በፆተኝነት የሰጠኋቸው ነገሮች የእውነታው አንፀባራቂ አይደሉም። ለብዙኃኑ ይሠራል ማለት ለሁሉም ይሠራል ማለት ስላልሆነ። ፆተኝነት ፆታዊ መድሎ የፈጠረው ስርዓተ ማኅበር መገለጫ ነው። ያንን ነው ለማሳየት የሞከርኩት። ምንጩን ስትጠቅስ ተሳስተህ ውጤቱን ነው የገለፅከው የሚለው ትችት ስለሃይማኖት በጻፍኩት ላይ ቢሆን ኖሮ ሚዛን የድፋ ነበር። ነገር ግን የሃይማኖቶች ጉዳይ ፆተኝነትን ተቋማዊ ማድረጋቸው ነው ለዚህ ትውልድ የፆተኝነት ምንጭ የሚያሰኛቸው።

ኢምንት ነገሮች ላይ ያተኮርኩት ፈረንጆቹ እንደሚሉት "ዘ ዴቭል ኢዝ ኢን ዘ ዲቴይል" ብዬ ነው። ትችቴ በያንዳንዷ ጥቃቅን ነገር ሳይቀር እንድንጠነቀቅ ነው። ጥቃቅኗ ተጠራቅማ ነውና ትልቁን የምተወፈጥረው።

የተፈጥሮ ልዩነቶችን አልተቃረንኩም። ነገር ግን ተፈጥሮም እንከን አልባ ናት ብዬ አላምንም። ማረም በምንችለው እና በምንፈልገው ልክ እናርማታለን። BefeQadu Z Hailuhttps://www.blogger.com/profile/10090745447582888476noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-5154675513695824940.post-74508196195663107722017-08-26T06:41:45.916-07:002017-08-26T06:41:45.916-07:00ይሄንን ፅሑ ሳነበው ልክ ሌሎች የሴቶችን የእኩልነት ጥያቄ ደግፈው የሚጻፉ ነገር...ይሄንን ፅሑ ሳነበው ልክ ሌሎች የሴቶችን የእኩልነት ጥያቄ ደግፈው የሚጻፉ ነገር የራሳቸውን አላማ ለማሳኪያ የሚጠቀሙበት ወይም የሴቶች እንቅስቃሴ በብዙሃኑ ተቃውሞ እንዲገጥመው እያደረጉ እንዳሉ ፅሁፎች እየተናደድኩኝ ነው የጨረስኩት። ምን ይበጃል ብለህ ያስቀመጥካቸው ነጥቦች እኔም ምስማማባቸው ነው በርግጥ ። ያናደዱኝ እና ያልተስማማሁባቸው ነጥቦች
1- ምክንያት ላይ ሳይሆን ውጤት ላይ ያተኮረ ሐተታ ነው የቀረበው
ፆተኝነታችንን ለማሳየት የተጠቀምቅባቸው ምሳሌዎች ማህበረሰቡን ለመውቀስ ነው እንጂ ያ እንዲሆን ያደረገውን ነገር ለማሳየት ፈፅሞ ማይጠቅም ነው። ለምሳሌ “ ሆስፒታል ሔደን ነጭ ጋዋን የለበሰች ሴት ስትገጥመን [ነርስ እንደሆነች እርግጠኛ በመሆን] "ሲስተር" የምንላት፣ ነጭ ጋዋን የለበሰ ሲገጥመን "ዶክተር" የምንለው የተዋሐደን ፆተኝነት አስገድዶን ነው“ ብለሃል። ይሄን አስተሳሰብ የፈጠረው መሬት ላይ ያለው እውነታ እንጂ ፆተኝነታችን አይደለም። እዚህ ላይ ሊያንገበግበን እና ልናተኩርበት የሚገባው ምን ያክሉ ሴቶች እየፈለጉ ነገር ግን እኩል ዕድል ሥላልተሰጣቸው እዚህ ቦታ ላይ ሳይደርሱ ቀሩ ሚለው ነው እንጂ ከ 50% በላይ ትክክል የመሆን ዕድል ባለው ነገር ሰዎች አመለካከታቸው ያንን እውነታ ይዞ ቢቀረፅ ፆተኞች ልንላቸው አይገባ። በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ያስቀመጥቃቸው ምሳሌዎች እኔ እንደዚህ ነው ምረዳው። እውነታ ይሄ ሆኖ ሳለ ሰዎችን በግድ እንዲህ አታስቡ ብሎ መውቀስ ተገቢ አይደለም። እውነታውን ከቀየርን በኋል ግን ይሄን አመለካከቱ ይዞ ሚገኝ ሰው ካለ ወይም ሴት ይሄን መሆን አትችልም የሚል አመለካከት ያለውን ሰውን ነው ፆተኛ ብለን ልንገልፀው የሚገባን።
2-ሴት ልጅ መብት እንጂ ግዴታም እንዳለባት አያሳይም
ስለመደፈር ያነሳኸውን እንደምሳሌ ብንወስድ እኔ ስለደፋሪው በምንም መልኩ ፈፅሞ አልከራከርም መቶ ፐርሰትን ጥፋተኛ ነው መቀጣት አለበት ። ማንም ሰው ሌላ ሰውን ያለፍላጎቱ አስገድዶ ፍላጎቱን እንዲፈፅም የማድረግ መብት የለውም ይልቁንም ሴትን አስገድዶ መድፈር ከወንጀልም በላይ ወንጀል ነው። ነገር ግን ይህን የሚያደርግ ሰው ፈፅሞ እንዲጠፋ ማረግ እስካልቻልን ድረስ ሴቷም ለእንደዚህ አይነት ነገር ከሚያጋልጧት ቦትዎች ፣ ሰዎች፣ ሁኔታዎች እራሷ እንድትጠብቅም ልንነግራት ይገባል። የሌለ ሀሳባዊ ዓለም እየሳልን ማቅረብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ነገር ግን ይህን ስል በምንም መልኩ ሴትን ለደፈር ይሄ እንደምክንያት ቀርቦ መከራከሪያ ሊሆንለት አይገባም። ሁላችንም በሕይወት ሥንኖር ፈተና ሚሆኑን የተለያዩ ነገሮች አሉ እነዛን ፈተናዎች ምናልፍበት እና እራሳችንን ምንጠብቅበት ጥበብ ያስፈልገናል። ስለዚህ ለሴቷ ይህን እውነታ ልንነግራት ይገባል። በተጨማሪ ሴት ልጅ እንደ አንድ የማህረሰብ አባል ሚጠበቁባት ግዴታዎችም አሉ።
3-መሰረታዊ ያልሆኑ ወይም ኢምንት ሚባሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል
የወንዶቹን ሥም አስቀድሞ መጥራት በእውነቱ አሁን ይሄን ያክል ትልቅ ጉዳይ ነው። መፍትሄ ሊሆን የሚችለው እንግዲህ ለቀሩት ዘመናት የሴቷን ማስቀደም ነው :) ወይም በየተራ መጥራት። እኔ እንደ አንድ ለመብቷ እንደምትታገል ሴት የምረዳው ይሄ ሃሳብ ትግሉን አቃሎ እንደሚያሳይ ነው። ትልቅ ሥራ የሚጠበቅበት መሰረታዊ ያልሆኑ ጉዳዮች ላይ ጉልበትም ጊዜም ሊያባክን አይገባውም። መሆን የምፈልገውን ነገር እንዳልሆን በሴትነቴ ብቻ ብዙ ተፅኖ የሚያደርጉብኝ፣ ሕልሜን እነሱ በመጠኑት ልክ አርገው ሊያሳዩኝ የሚሞክሩ አስተሳሰቦችና ሁኔታዎች እየታገልኩኝ እንደዚህ አይነት ነገሮች ጉዳየም አርጌ አላየውም (ጉዳይም የሚደረጉም አይደሉም)። እንደዚህ አይነት እርባና ቢስ ነገሮችን ከሴቶች የ እኩልነት ጥያቄ ጋር አያይዘን ማንሳታችን እንቅስቃሴውን ሰዎች አቅለው እና በንቀት እንዲያዩት ያረጋል እንጂ ምንም ጥቅም የለውም። ዋና የሴቶች ጥያቄ በስርአት ማስተላለፍ ብንችል አሁን የምናያቸውን ተቃዋሚዎች እና በፍረሃት የሚመለከቱቱን ሰዎች የእንቅስቃሴው አካል ማድረግ እንችል ነበር።
4- ሌሎች
አሁን ያለው የማህበረሰቡ አመለካከት የተመሰረተበት በፊት የነበሩ የኑሮ ሁኔታዎች ላይ ነው። ድሮ በነበረው አኗኗር ይመቻል ያሉትን ሥርአት ሰርተዋል ጥያቄአችን ድሮ ለምን እንዲህ ሆነ ሳይሆን ዛሬ ነገሮችና ሁኔታዎች ስለተቀየሩ የ ሴቶችን ኑሮ እና ሚና በዛ ልክ በተሰፋው አስተሳሰብ አይቀረፅ ነው። ወንዱ እንደብቻ የገቢ አስገኚ ተደርጎ ቢቆጠር ከሴት ይልቅ ወንዶች አድነው አርሰው ቤተሰባቸውን ይመግቡ ነበር ይህ ሀቅ ነው። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ሴቶች በሁሉም መስክ ከወንድ እኩል ድርሻ መውሰድ ስለሚችሉ ያ አስተሳሰብ ይቀየር ነው ጥያቄው። ኑራችንም ይህን መሰረት አርጎ ይዋቀር ነው። ማለት የፈለኩት ምንድነው የዱሮውን መውቀስ ላይ ሳይሆን ዛሬን መቀየር ላይ ነው ትኩረታችን መሆን ያለበት።

የተፈጥሮ ልዩነቶችን መቀበል አለብን፣ የተያዘው የመበት ትግል እንጂ ልቅነትን መስበክ አይደለም። ሴቶች ከወንዶች በተፈጥሮ ምንለይባቸውን ነገሮችን መቀበል አለብን ይሄ ልዩነታችን ፀጋ ነው ያለበለዚያማ ሴት እና ወንድ ሆነን መፈጠር ባላስፈለገ ነበር። ወሲባዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ለሴቶች የተለዩ የሚመስሉ መስመሮች የተሰመሩ ያነሳሃቸው ነገሮች አሉ ። እኔ እንደምረዳው በተፈጥሮ ምክንያት ከወንዱ ይልቅ ሴቷ ላይ የሚከተለው ውጤት ከባድ ስለሆነ ነው። ያልተፈለገ እርግዝና፣ ውርጃ ተከትሎም ልጅ መውለድ እንዳትችል የሚያደርጋት ሁኔታ፣ ከሚወሰዱ መድሃኒት የተነሳ የሚመጡ ሌሎች ችግሮች ፣ ወዘተ ይሄ ሁሉ ነገር እያለ ሴቷም እንደፈለገች ትሁን ብሎ መስበክ ጉዳቱ እንጂ ጥቅም የለውም። የሴቶች እንቅስቃሴም አላማው ይሄ አይመስልኝም። ሃይማኖትን የተመለከቱ ያነሳሃቸው ነጥቦች አንተ ባላህ የአረዳድ ልክ ነው ያቀረብከው ብዙም ማለት አልፈልግም።
ባጠቃላይ የሴቶችን የመብት ጥያቄ ደግፈህ መፃፍህ በራሱ የሚበረታታ ነው። ቢሆንም የተፃፈው ፅሁፍ ወጤቱ አንተ ባሰብከው መልኩ ደጋፊ ሣይሆን ታቃዋሚ ሚያበዛ ነው። መቼም አንተም እንደምታስተውለው ብዙዎች ፌሚኒዝም የሚፈሩት ና በአይነ ቁራኛ የሚያዩት ዋናውን አላማ በደንብ ከማቅረብ ይልቅ በኛ ግላዊ የሃይማኖት፣የኑሮ መርህ ወዘተ ለውሰን ስለምናቀርበው ነው። ስለዚህ አንተ ፅሁፍህ መግቢያ ላይ እንደተማፀንከው እኔም እባካችሁ ስለፌሚኒዝም ስትፅፉ የራሳችሁን የሃይማኖት፣ የባሕል፣ የፖለቲካ አቋም ደባልቃቹ አትፃፉ ብዬ ተማፅኖየን አቀራብለሁ።
Anonymousnoreply@blogger.com