Skip to main content

Posts

Showing posts from 2017

The Sensational OPDO and Popular Reactions

(A note inspired by a Facebook post of Yemane Mitiku) The people in social media and beyond are perplexed about what is going on within EPRDF. Almost all assumptions are made based on the news that reached the public from what is happening behind closed doors. However, it can be reached at a point where we can be sure there is internal struggle which is manifested in a lot of issues that resulted in personal cults of team Lemma Megersa of OPDO and sometimes Gedu Andargachew of ANDM. Herebelow, I put what I have observed from commentators why people appreciate the sensational progress OPDO in standing against widely accepted TPLF's supremacy as well as why they reject it. Who Rejects Team Lemma and Why? 1. Those cadres who want to protect TPLF's supremacy within EPRDF and the Federal State; 2. Those OPDO cadres who want to submit to TPLF and replace current leaders of OPDO; 3. Those activists who don't know political games apart from their hates to ...

#QilintoFire case victims responded to EHRC report

On 11th of October 2017, the State-run Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) has written the long awaited  report  of its investigation of rights violation against  Qilinto Fire  defendants as per the request of the 19th Bench of Federal High Court at Lideta. On the five pages of report, EHRC revealed scars left after tortures during investigation against 16 defendants among 38 people charged under the same case. The report also revealed flogging marks left on the defendants’ backs, breaking of fingers, scars left after nail-pierced body parts and uprooted finger nails of multiple defendants. Here below I will jot down the torture scars listed in the report and will follow what the defendants have written in response: Kebede Chemeda – a scar on his right hand; breaking in his right hand thumb Ibrahim Khamil – a scar on his right leg; a scar on his left hand; scar-marked left from handcuffs Agbaw Setegn – large scar on his left leg thigh; a scar on his right ...

What if We Were Raised with an ‘Authoritarian Personality’?

We less often discuss personalities that are fertile grounds either to be ruled by authoritarians or to be one of them. But, I think, it is important to look what is in them as it looks like we dont basically change from the way our parents have raised us. Our ancestors were either members of the oppressors or the majority (the oppressed) in the past, so are we. It happens to be we use that same privilege inherited from our parents to advance others; or, to remain underprivileged. History proves it is most probable that off springs follow their ancestors footsteps. Chances are big that children of the poor will remain poor; children of farmers remain farmer; children of democratic societies will remain democrat and etc. And, all this is until the quagmire breaks at some point. What's keeping us a conformist? And, how can we break it? I was reading a book titled "Between the World and Me" authored by Ta-Nehisi Coates and found some childhood experiences were shar...

ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ይልቅ ኢሕአዴግን ያምኑ ይሆን?

ከዓመታት በፊት አንድነት ፓርቲ በሕይወት ሳለ፣ የቀድሞዎቹ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት አቶ ስዬ ኣብርሓ እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲውን ሊቀላቀሉ ሲሉ ትልቅ ፌሽታ ሆኖ ነበር። እንዲያውም ‘መርሕ ይከበር’ በሚል የተገነጠለው ቡድን፣ እነርሱን ለመቀበል የተዘጋጀውን ድግስ በአመፅ እስከማደናቀፍ ደርሷል(?)። ቅራኔው “እነርሱ የተለየ አቀባበል የሚደረግላቸው የገዢው ፓርቲ የቀድሞ አባል ስለሆኑ ነወይ?" የሚል ነበር። ተቃዋሚው የቀድሞ የኢሕአዴግ አባል ለቅቆ ሲወጣ ማግነን ያውቅበታል። በአንድ በኩል ሳስበው፣ መቃወማቸው ትክክል መሆኑን የገዢው አባላት መልቀቅ ለተቃዋሚዎቹ ስለሚያረጋግጥላቸው ይመስለኛል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ከጥቅም ባሕር ውስጥ መውጣት ስለሚከብድ ያንን እያሰቡ ይመስለኛል። የኋለኛውን እንዳላምን እንደ ዶ/ር ነጋሶ፣ ከጥቂቶቹ በቀር ብዙዎቹ ተገፍተው ነው ከገዢው የሚወጡት። የሆነ ሆኖ፣ አናንያ ሶሪ በስላቅ እንደተናገረው፣ ‘ብለን ብለን ኦሕዴድ እና ብአዴን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ዛሚ እና ENN ነጻ ሚድያዎች የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል’። ለማንኛውም በምናገባኝ ነገሩን ከመታዘብ ይልቅ የኦሕዴድ (እንዲሁም የብአዴን) የሰሞኑ እምቢተኝነት እውነት ወይስ የሕወሓት ሴራ? ተቃዋሚው (በፓርቲ የታቀፈውም ያልታቀፈውም) ጉዳዩን እንዴት ነው ማስተናገድ ያለበት? የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክር። የጠላቴ ጠላት ለኔ ምኔ? በተቃዋሚዎች ዘንድ "የሕወሓት የበላይነት" መኖሩ እምብዛም አጠራጣሪ አይደለም። ማኅበራዊ ሚድያ አሁን (ከተዳራሽነቱ በላይ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሐሳብ አቅጣጫ አስማሪ እንደመሆኑ ይህንን እምነት የበለጠ በማስረፅም ሆነ በመታገል ረገድ የጉዞ ካርታ (road map) አስቀማጭ ነው። ይህንን ብዙዎች መረዳታቸው ሽሚያ ...

ማነው አሳሪ? ማነው ፈቺ?

አግባብ ያልሆኑ እስሮች፣ ያልተጠበቁ ፍቺዎች እና የማይታመኑ የፍቺ ክልከላዎች ደጋግመው ቢከሰቱም ሁሌ እንደ አዲስ የሚያወያዩን አጀንዳዎች ናቸው። ኦቦ በቀለ ገርባ የታሰሩት የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ ያለ ፍርሐት ስላስተጋቡ ብቻ ነው። ይህን የምለው ለይስሙላ አይደለም፤ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን ማስረጃ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ አራተኛ ወንጀል ችሎት ተገኝቼ አድምጬያለሁ። ችሎቱ ክሳቸውን ከሽብር ወደ 'በንግግር አመፅ ማነሳሳት' (የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 257/ሀ) ዝቅ ሲያደርገው ዋስትና እንደሚያሰጣቸው ግልጽ ነበር። ችሎቱ በዋስትና ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት ከአንድ ቀጠሮ በላይ ሲወስድ አይቼ አላውቅም። እርሳቸውን ግን ደጋግሞ ቀጠሮ ሲሰጣቸው፣ ዳኞች ዋስትናውን መከልከልም ሆነ መፍቀድ የፈሩ ይመስል ነበር። በመጨረሻ የሞት ሞታቸውን ከለከሏቸው እና አረፉ። ይግባኝ ተባለ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ30 ሺሕ ብር የስር ፍርድ ቤት የከለከለውን ፈቀደ። ቂሊንጦ እስረኛ ማቆያ ቤት እስረኛውን በመፍታት ፈንታ ደብዳቤው ላይ የተጻፈው ቁጥር አደናገረኝ በሚል ሰበብ ሁለት ቀን አሳደራቸው። በመሐል ፋና ሬዲዮ የኦቦ በቀለ ፍቺ በዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ባይነት፣ በሰበር ሰሚ ችሎት ታገደ የሚል ዜና ይዞ ወጣ። Déjà vu.  ሐምሌ ወር 2007፣ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃም ሰለሞን ነጻ ከተባሉ በኋላ የተከሰተው ይሄንኑ ይመስል ነበር። ቤተሰቦቻቸው ሲፈቱ ለመቀበል ቂሊንጦ በር ላይ ሲመላለሱ፣ ማረሚያ ቤቱ ሰበብ ሲፈጥር አቆያቸው፤ በመሐል፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍቺያቸውን እንዳገደው ተሰማ። ከዚያ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በዞን ዘጠኝ ጉዳይ ከታሰሩት አምስቱ ድንገት ስማቸው ተጠርቶ...

የምርጫ ስርዓቱ መሻሻል ጉዳይ

ብዙ ሰው ችላ ብሎታል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ግን "መደራደራቸውን" ቀጥለዋል። ከኢሕአዴግ ጋር እየተደራደሩ ያሉት ፓርቲዎች ምንም ሕዝባዊ ቅቡልነት/ውክልና የላቸውም ማለት ይቻላል። ለዚያ ነው "ድርድሩ" ጆሮ ያጣው። ዞሮ ዞሮ ኢሕአዴግ "ድርድሩን" ሲጠራ በተነሳበት ዓላማ ሊጠናቀቅ ተዳርሷል። የምርጫ ስርዓቱን ማሻሻል። ኢሕአዴግ ውጤቱን "በድርድር" የተገኘ ለማስመሰል ስለፈለገ እንጂ ቀድሞውንም ስርዓቱን ለማሻሻል ወስኗል። ለምን እና እንዴት? ፩) ቀዳሚ አሳላፊ (First Past The Post /FPTP) የተባለው የአሁኑ ስርዓት ድምፅ አባካኝ ነው። ነገሩን በምሳሌ ለማስረዳት የምርጫ 2002 የአዲስ አበባ ውጤትን እናመጣለን። በወቅቱ ከመረጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ውስጥ 54% ኢሕአዴግን መረጡ፣ 37% መድረክን መረጡ፣ 9% ሌሎች ተቃዋሚዎችን መረጡ። ነገር ግን ከአንድ ተቃዋሚ በስተቀር ፓርላማ ባለመግባቱ በጥቅሉ የ46% የአዲስ አበባ መራጮች ድምፅ ባክኖ ቀርቷል። ፪) ብዙ መራጭ ባላቸው የምርጫ ክልሎች ብዙ ድምፅ ያገኙ ተወዳዳሪዎች ሲወድቁ፣ ትንሽ መራጭ ባለባቸው የምርጫ ክልሎች ያሉ ተወዳዳሪዎች ባነሰ ድምፅ አልፈዋል። ለምሳሌ በዚያው የ2002 ምርጫ ወቅት በአንድ የምርጫ ክልል 42,555 ድምፅ ያገኙት የመድረክ ተወዳዳሪ አቶ ዑርጌሳ ዋኬኔ ፓርላማ አልገቡም፤ ነገር ግን በሌላ ምርጫ ክልል 12,753 ድምፅ ያገኙት የኢሕአዴግ ተወዳዳሪ ዶ/ር እልፍነሽ ኃይሌ ፓርላማ ገብተው ነበር። ፫) የምርጫ ስርዓቱ ተመጣጣኝ ውክልና (proportional representation /PR/) ቢሆን ኖሮ ለአዲስ አበባ ከተተዉት 23 የምክር ቤት ወንበሮች ውስጥ 12ቱ በኢሕአዴግ፣ 9ኙ በመድረክ እና ቀሪዎቹ ሁለቱ ለሌ...

የባንዲራ ማኒፌስቶ!

ልጅ እያለን፣ ታላላቆቻችን እኛን እርስበርስ እያደባደቡ ሲዝናኑብን እንዲህ ያደርጉ ነበር። ምራቃቸውን መሬት ላይ ሁለት ቦታ ላይ እንትፍ እንትፍ ይሉና፣ "ይቺኛዋ ያንተ እናት፣ ያቺኛዋ ደግሞ ያንተ እናት ናት" ይሉናል። ከዚያም "ማነው የማንን እናት የሚረግጠው?" ሲሉ፣ አንዱ ቀድሞ የሌላኛውን "እናት" (በትፋት የራሰውን አፈር) ከረገጠ ድብድቡ ይጀመራል። የተተፋበትን አፈር የረገጠውን ልጅ ዝም ማለት፣ እናትን አስረግጦ ዝም እንደማለት ነበር የሚቆጠረው። የውርደት፣ የሽንፈት ስሜት አለው። በልጅነት ዐሳባችን የእናታችንን ትዕምርታዊ መገለጫ ማስደፈር እናታችንን ከማስደፈር ዕኩል ስለሚሰማን ወትሮ ከማንደፍረው ሰው ጋር ሳይቀር እንጋጫለን። የባንዲራ ትዕምርትም እንደዚሁ ነው። ሰንደቅ ዓላማ የአገርና የአገራዊ ፖለቲካ አስተሳሰብ ትዕምርት (‘ሲምቦል’) ነው። ሁለት አገራት ወደጠብ ሲገቡ በሕዝባዊ ተቃውሞ ሰልፎች ላይ ባንዲራ ማቃጠል፣ በፊት በፊት ፋሽን ነበር። አሁንም ድረስ ባንዲራ የማቃጠል ተቃውሞ አለ። የባንዲራ ትዕምርታዊነት ሰፊ በመሆኑ ቬክሲሎሎጂ የሚል የጥናት ዘርፍ ተቋቁሞለታል። በባንዲራ መከባበርም፣ መናናቅም ይገለጻል። ሕዝባዊ ሐዘን ይገለጽበታል። ደስታ ይበሰርበታል። የአገር ፍቅር ልክ ይመዘንበታል። “ከብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን” ባሻገር! አቶ መለስ "ባንዲራ ጨርቅ ነው” ብለው ሲናገሩ የሳቱት ጉዳይ ይህንን ትዕምርታዊ ውክልናውን ነው። በርግጥ ይህንን አሉ በተባለበት ወቅት አገሪቱ ከአንድ ይፋዊ ሰንደቅ ዓላማ ወደ በርካታ ባንዲራዎች እየተሸጋገረች ስለነበር፣ "ባንዲራ ጨርቅ" ብቻ ከሆነ ያንን ሁሉ ለውጥ ለምን ማድረግ እንዳስፈለጋቸው መጠየቅ ነበረባቸው። አቶ መለስ ይህንን ...

የአማራ ብሔርተኝነት እንቆቅልሽ (የመቋጫ መጣጥፍ)

"የአማራ ሥነ ልቦና" በሚል ርዕስ ቀደም ሲል የጻፍከት አጭር የእንግሊዝኛ መጣጥፍ ብዙ ጥያቄዎችን አጭሯል። የጽሑፉ ዋነኛ ዓላማ ስለአማርኛ ቋንቋ ዕድሜ፣ ወይም ስለአማራ ሕዝብ ኅልውና ባይሆንም፣ ብዙዎቹ አንባቢዎች ግን የተረዱት በዚያ መንገድ ነበር። ወሳኙ ቁም ነገር እኔ የጻፍኩበት ዓላማ ሳይሆን አንባቢ ጋር ሲደርስ የሰጠው ስሜት ስለሆነ ይህንን ጽሑፍ አስከትያለሁ። በመሠረቱ፣ ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደገለጽኩት፣ እኔ የምፈልገው ዘውግ-ዘለል የዜግነት ብሔርተኝነት (civic nationalism) ነው፡፡ ይህን ስል ግን የዘውግ ብሔርተኝነትን እና በዘውግ መደራጀትን እቃወማለሁ ማለቴ አይደለም፤ በዘውግ ላይ የተመሠረቱ ጥያቄዎች እስካሉ ድረስ ያንን በመከልከል ማስቆም ይቻላል ብዬ አላምንም፡፡ ነገር ግን የተለያዩ የዘውግ ቡድኖችን እና ፍላጎቶቻቸውን አቻችሎ በአንድ ለማኖር የዜግነት ብሔርተኝነት ማበበ አለበት ባይ ነኝ፡፡ ይሁን እንጂ ብዙዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች በዘውግ ስለተዋቀሩ እና የመንግሥታዊ አደረጃጀቱም ይህንን (ለዜግነት መብቶች በርዕዮተዓለም መደራጀት) ምቹ ሁኔታ ስላልፈጠረለት አገሪቷ የፉክክር ቤት ሆናለች። ስለሆነም፣ ይሔ እና መሰል ጽሑፎች፣ በአገራችን የተንሰራፋው በአሁኑ ወቅት የበለጠ ተቀባይነት ያለው የዘውግ ብሔርተኝነቱ አካሔድ ቢያንስ ወደፊት ወደ ዜግነት ብሔርተኝነትን እንዲያድርግ የማደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ይታወቅልኝ። አሁንም ከዚህ በፊት "የተጣመመ የብሔርተኝነት ቅርንጫፍ" በሚል የኦሮሞ ብሔርተኝነት አራማጆች ላይ አስተዋልኩት ብዬ የጠቃቀስኩት የጠራ ዘር እና የዘር ሐረግ በመቁጠር ላይ የተመሠረተ ብሔርተኝነት አዝማሚያ “ገና አፍላ ነው” በሚባለው የአማራ ብሔርተኝነት ላይም በጉልህ ያስተዋልኩ ...

የአራማጅነት ሀሁ…

‘አክቲቪዝም’ በአማርኛ ቁርጥ ትርጉም አልተገኘለትም። እንዲሁ በየዐውዱ "የለውጥ አራማጅነት"፣ "የመብቶች አቀንቃኝነት"፣ ወዘተ… ነው የሚባለው። የእንግሊዝኛ ቃሉን ግርድፍ ትርጉም ከወሰድን "ንቁ ተሳታፊ" ከሚለው የሰፋ ትርጉም የለውም። በኢትዮጵያ ቃሉ በተደጋጋሚ መደመጥ የጀመረውና ራሳቸውን ‘አክቲቪስት’ ብለው የሚጠሩ ሰዎች የተከሰቱት ከማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ማደግ ጋር ተያይዞ ነው። በተለምዶ፣ ቃሉ በጥቅሉ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያደርጉ እና የሚወክሉት ድርጅት የሌላቸውን ግለሰቦች በሙሉ ለመግለጽ እየዋለ ነው። እዚህ ጽሑፍ ላይ የምጠቀምበት ገላጭ ሆኖ ያገኘሁትን "አራማጅነት" የሚለውን ቃል ነው። አራማጅነት ምንድን ነው?  አራማጅነት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና/ወይም አካባቢያዊ ለውጦችን ለማምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። አራማጅነት የአጭር ግዜ ፕሮጀክት ወይም ዘላቂ ንቅናቄ ሊሆን ይችላል። አንድ ጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ ወይም ብዙ ጉዳዮችን ያቀፈም ሊሆን ይችላል። አራማጅነት በብዙኃኑ ተቀባይነት ያለውን አንድ ጉዳይ በመንግሥት ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ወይም በመንግሥት ዕውቅና ያለውን ጉዳይ በብዙኃኑም ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ወይም በብዙኃኑም፣ በመንግሥትም ተቀባይነት እና ዕውቅና የሌለውን ጉዳይ በሁለቱም ተቀባይነት እና ዕውቅና እንዲያገኝ ለማድረግ ሊሆን ይችላል። አራማጅነት በብዛት ከተገለሉ ሕዳጣን ወይም ከተጨቆኑ ብዙኃን መሐል በወጡ አራማጆች የሚደረግ የመብት/የጥበቃ ንቅናቄ ነው። የአራማጅነት ስኬት እንደመነሻው ነው የሚለካው። አንዳንዴ የተነሳውን ሐሳብ የተደራጁ ሲቪል ማኅበረሰቦች ወይም የፖለቲካ ማኅበሮች አጀንዳዬ ብለው ሲይዙት ከአራማጆች እጅ ሊወጣ ይችላል። ሌላ ግዜ ደ...

How Much Do You Know About (mis)use of Ethiopia’s Anti-terrorism Proclamation?

Many often fail to imagine the subjective consequences of public actions. Here I want you to imagine personal crises with the numbers I will follow. As a living victim of (mis)use of the Anti-terrorism Proclamation (ATP) in Ethiopia, I face a heartbreaking judgement oftentimes from ordinary citizens who knew that I was once charged of the ATP. They say, "you must have been involved in ‘something’ that got you suspected of terrorism". I find it difficult to explain how the ATP became a tool to stifle dissent in the country. This, however, is not my personal problem, it is a challenge of many others; nor it is the only problem, there are a lot of sufferings it caused. Once someone is charged of Ethiopia’s ATP, her/his life will turn upside down. It is mostly difficult for ex-suspect/convict of the infamous ATP to get one’s job back nor to find a new one; the blank space in one’s CV sounds to employers like “don’t give them the job, otherwise you will draw government spies...

ኢትዮጵያ ያለ«ኢትዮጵያዊነት» ልትኖር አትችልምን?

በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በጣም ተወዳጁ ኤፍኤም ሬዲዮ ሸገር ነው ቢባል የሚያጣላን አይመስለኝም። ሸገር መፈክሩ "ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር" የሚል ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፖለቲከኞችም ይህንኑ መፈክር የንግግራቸው ማሳረጊያ ዓረፍተ ነገር እያደረጉት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ከመግለጫዎቹ ግርጌ “ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር” የሚል ዓረፍተ ነገር ያስቀምጣል። አዲሱ በእነሰይፉ ፋንታሁን እና ሠራዊት ፍቅሬ… የተከፈተው ኢትዮ ኤፍኤም ሬዲዮ "ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ" የሚል መፈክር ይዞ መጥቷል። በቅርብ ጌዜ ከተከፈቱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አንዱ - ጄቲቪ - መፈክሩ "ኢትዮጵያዊነት መልካምነት" የሚል ነው። "ኢትዮጵያ" የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ዘፈን የአገር ውስጥ ሽያጭ ሪከርድ ሰብሯል። የሐበሻ ቢራ ማስታወቂያ ‘ኢትዮጵያዊነት’ የሚለውን ቃል ማዕከል ያደረገ እና ስለኢትዮጵያ ‘ገናና ታሪክ’ የሚያወሳ ዓይነት ነው። ሐበሻ ቢራ ገና ከመተዋወቁ ገበያው ደርቶለት የነበረውን ዋልያ ተቀናቅኖ ወጣ። ገበያው ከማስታወቂያው ነው ብለው ይመስላል፣ ሌሎቹም ቢራዎች ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው ማስታወቂያዎችን ይዘው ብቅ-ብቅ ማለት ጀመረዋል። የቴሌቪዥን ትዕይንቶች፣ የግጥም ምሽቶች፣ ሌሎችም የጥበብ ሥራዎች ከመቼውም ግዜ በላይ ‘ኢትዮጵያዊነት’ን እያንቆለጳጰሱ ነው። በምላሹም ቀላል የማይባል ጭብጨባ ይቀበላሉ። እነዚህ ሁሉ በተለምዶ "ኢትዮጵያዊነት" የሚባለው የአንድነት ኃይሉ ፖለቲካዊ ንቅናቄ ማኅበራዊ መገለጫዎች ይመስላሉ። ነገር ግን እነዚህ ይፋዊ መፈክሮች “ንቅናቄው እያደገ መምጣቱን ያረጋግጣሉ ወይስ፣ የዘውግ ፖለቲካ ንቅናቄ እና ዕድገት ድንጋጤ የፈጠረው ግብረ መልስ ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አስፈላጊ ነው። ...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...

የተዋሐደን ፆተኝነት

ይህ ጽሑፍ ስለ ፍትሕ ነው። አንባቢዎቼን በትህትና አስቀድሜ የምጠይቀው ነገር ቢኖር የፆታ፣ የሃይማኖት፣ የባሕል፣ የፖለቲካ ወገንተኝነት መነፅሮቻችሁን አውልቃችሁ በፍትሕ መነፅራችሁ እንድታነቡኝ ነው። የተዋሐደን ፆተኝነት ስንል ምን ማለታችን ነው? ምንጮቹ ምን ምን ናቸው? ውስጣችን ያለው ይህ ፆተኝነት ምን ያህል ችግር ይፈጥራል? የተዋሐደንን ፆተኝነትን እንዴት እንቅረፈው? መግባቢያ ስለፆተኝነት ፆተኝነት ማለት በአጭሩ ‘ፆታዊ መድልዖ’ ማለት ነው። በዓለማችን እጅግ የተንሰራፋው ለወንዶች የሚያደላው ወይም አባታዊው ስርዓተ ማኅበር ነው። (እርግጥ እጅግ ጥቂት ሆኑ እንጂ እናታዊ ስርዓተ ማኅበሮችም አሉ፡፡ ለምሳሌ ሕንድ አገር ሜጋላያ ስቴት ውስጥ የሚገኙት ጎሳዎች ሀብት የሚተላለፈው ከእናት ወደሴት ልጅ ነው፡፡ በዚህ ስርዓተ ማኅበር የትምህርትና መሰል ዕድሎች ከወንዶች ይልቅ ለሴቶች ይመቻቻሉ፡፡ ይህን ምሳሌ በዓለም ከተንሰራፋው አባታዊው ስርዓት አንፃር ከቁብ ሳልቆጥረው ላልፍ እችል ነበር። ነገር ግን የእነዚህ ጎሳዎች እናታዊ ስርዓት ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ እዚህ መድረሱ አባታዊው ስርዓትም ሆነ እናታዊዋ በማኅበራዊ ብሒል የሚገኙ እንጂ ተፈጥሮ ያከፋፈለችን ሚና አለመሆኑን ስለሚያሳይ ነው።) የአገራችን ስርዓተ ማኅበር ከጥግ እስከ ጥግ አባታዊ ነው። ይህንን ስርዓተ ማኅበር ለመቀልበስ እና ፍትሐዊ ስርዓተ ማኅበር ለመመሥረት የሚደረጉ የተደራጁም ይሁን ያልተደራጁ ንቅናቄዎችን ሴታዊነት እንላቸዋለን። (‘እንስታዊነት’ የእንግሊዝኛውን ‘Feminism’ በቀጥታ የሚተካ ቢሆንም፣ አማርኛችን ስርዓተ ፆታ (gender) ያልተጫነው ‘ሴት’ የሚል ሥነ ተፈጥሯዊ (biological) ልዩነቱን ብቻ የሚገልጽ ቃል ስላለው ‘ሴታዊነት’ የሚለውን መርጫለሁ። በዚህ ጽሑፍ ውስ...

"ዘውጌኝነት" እና "ዘውግ-ዘለልነት"…?

የዘውግ ብሔርተኝነትም ይሁን ኢትዮጵያዊ ኅብረብሔርተኝነት አተያዮች በዘውግ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ሁለቱም ዜጎችን የሚመለከቱት የዘውግ ምንዝር (ethnic subjects) አድርገው ነው። ስለዚህ ይለያያሉ ማለት አይቻልም። ለብዙዎቹ ችግሮቻችን ፍቱን መድኃኒት አድርጌ የምወስደው፣ ጉዳዩን በዘመን ቁመት እና በዓለም ሕዝቦች ታሪክ አግድም መመልከት ነው። ዓለም በበቂ ሁኔታ የምንማርባቸው ስኬቶች እና ውድቀቶች አሏት። ዘውጌኝነት፣ ብሔርተኝነት እና ዜግነት የመሳሰሉትም የብቻችን ጉዳዮች አይደሉም። ዓለም በየፈርጁ የዳከረችበት እና እየዳከረችበት ያለ ችግር ነው። ስለዚህ ጥያቄውን በቅጡ ለማበጃጀትም ይሁን፣ አዋጭ መልስ ለመፈለግ ከሰው ልጆች እንደአንድ የሚያደርገንን ታሪክ የምናውቀውን ያክል ማሰስ ያስፈልጋል። ይህን ከጠቆምኩ በኋላ ወደ የበኩሌን ለመሞከር ወደ አጀንዳዬ እዘልቃለሁ። የዘውግ ብሔርተኝነት ምንድን ነው? የዘውግ ብሔርተኝነት (ethnonationalism) የአንድ ዘውግ (ethnic) ቡድን ነጻ አገር እንዲመሠርት ወይም ከመገንጠል ወዲህ ያለውን የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ለማስቻል የሚደረግ ፖለቲካዊ ንቅናቄ ነው። የዘውግ ማንነት በኢትዮጵያ ልማዳዊ አሠራር በወላጆች ማንነት ነው የሚወሰነው። እናትና አባታቸው ከተለያዩ ዘውጎች የተወለዱ ዜጎች በተለምዶ የአባታቸውን የዘውግ ሐረግ ነው የሚወርሱት። ዜጎች በአንድ ክልል ተወልደው፣ የአካባቢውን ቋንቋ፣ ባሕልና ወግ አውቀው ቢያድጉም ከአካባቢው ዘውግ የተለየ ዘውግ ካላቸው ወላጆች ከተወለዱ የአካባቢው ዘውግ አላቸው አይባልም። ማለትም፣ ለምሳሌ በኦሮሚያ ከአማራ ልጆች ተወልደው ያደጉ ልጆች በዘውግ ብሔርተኞች እንደኦሮሞ አይቆጠሩም። በሕግ የመምረጥ እና መመረጥ መብት ቢኖራቸውም በልማድ ተቀባይ...

የቂሊንጦ እሳት፣ ወላፈኑን የቀመሱት እና በሰበቡ የተከሰሱት

(ፎቶ፤ ደህናሁን ቤዛ) ይህ ታሪክ በደርግ ዘመን የተፈፀመ አይደለም። በኢሕአዴግ ዘመን የተፈፀመ የበደል ታሪክ ነው።… የምነግራችሁ ታሪክ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ "ለተሀድሶ ሥልጠና" ወደ አዋሽ ሰባት የፖሊስ ካምፕ የተጓዝኩትን ያስታውሰኛል። "ከሥልጠናው" ሰነዶች በአንዱ ላይ፣ በደርግ ግዜ ይፈፀሙ የነበሩትን የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች "ሰምቶ ማመን የማይችል ትውልድ ተፈጥሯል" ይላል። አባባሉ የኢሕአዴግን በትር እየቀመሱ ለኖሩ በጣም ያስቆጣል። ቀጥሎ የማወራላችሁ ታሪክ የደናሁን ቤዛ ታሪክ ነው። ደናሁን ደርግን የማያውቅ ወጣት ነው። ኢሕአዴግን ብቻ እያየ አድጎ ኢፍትሐዊነቱን መቀበል ያቃተው የመርሃዊ፣ ጎጃም ልጅ ነው። ደናሁን በእነዘመኑ ካሴ በእውቄ መዝገብ፣ በፀረ ሽብርተኝነቱ አዋጅ ከተከሰሱት 9 ሰዎች 3ኛው ነው። ባለፈው ሳምንት የእስር ግዜውን ጨርሶ በፍቺ ተሰናብቷል። ከአባሪዎቹ መካከል አሸናፊ አካሉ በቂሊንጦ እሳት አነሳሽነት ክስ ተመሥርቶበታል። አንሙት የኔዋስ የተባለው ደግሞ ይህንን ለዐቃቤ ሕግ ከሚመሰክሩት መካከል ሥሙ ተጠቅሷል። ቁጥቡን ደናሁንን የተፈታ'ለት አግኝቼው ነበር። ብዙ ነገር ተጨዋወትን። ሸዋሮቢት ወስደው በካቴና አስረው ሰቅለው ሲገርፉት ካቴናው የእጁ ወርች ላይ፣ እግሩ የታሰረበት ገመድ ደግሞ ከቁርጭምጭሚቱ በላይ ያወጡትን ሰምበር እያሳየኝ ነበር። ይህ ድርጊት ከተፈፀመበት 9 ወር ገደማ ቢሆንም ጠባሳው እስካሁን ከሰውነቱ አልከሰመም። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ምንም ያልሠራውን ወንጀል ባለማመኑ ይመስላል፣ ወይም ደግሞ ምናልባት ሌሎች እስረኞች ሥሙን ስላልጠቀሱ ከጓደኞቹ ቀላቅለው አልከሰሱትም፤ አባብለው ምስክር እንዲሆንባቸውም ማድረግ አልቻሉም። የደናሁን ጀብ...

Captivity in the Name of ‘Defamation’!

(The origional version of this story is published in Amharic on Ethiopian Human Rights Project website.) The past year ended with two notable controversies between the press and Ethiopian Orthodox Church (EOC). The first one was concluded with a rare rule from an Ethiopian court that served justice to the press. The second one, undeservedly awarded the EOC a victory against a journalist who reported what happened, as it happened. The first was 100% critical comment against the patriarch of EOC who, according to the writer Daniel Kibret, is negligent when corruption is spread in the church. The latter is a news report (pictured below) that referred to a letter written by community and priests of St. Mary’s Church, which is also a seat for the EOC patriarch. The critical opinion written by the renown Daniel Kibret was published on Sendek newspaper; while, the news report was published on Ethio-mihidar newspaper, known for giving space to dissent voices of Ethiopia. Editor-in-c...

የረቂቅ አዋጁ ዓላማ ምንድን ነው?

“የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅምን አስመልክቶ የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ” የሚል  ባለ 46 ገጽ ሐተታ  እና በዚሁ መሠረት የተዘጋጀ  ረቂቅ አዋጅ  በኢንተርኔት ተለቀዋል፡፡ አዘጋጁ ኦሕዴድ የሚመራው የኦሮሚያ መንግሥት ነው ተብሎ ቢገመትም በኦፊሴላዊ መንገድ ስላልተለቀቀ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡ እስካሁን ድረስ ማስተባበል የነበረበት መንግሥታዊ አካል ስላላስተባበለ እና ከውዥንብሩ መውጣት ስላልቻልን እንዲሁም ረቂቁ ትችት ስለሚያስፈልገው፣ ረቂቅ አዋጁ ላይ የሰፈሩት አንዳንድ ጉዳዮች አሳሳቢነት ላይ ያለኝን አስተያየት አሰፍራለሁ፡፡ የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49/5 እንዲህ ይነበባል፣ “የኦሮሚያ ክልል፤ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ [የተነሳ] ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡” የረቂቅ አዋጁም በመግቢያው ላይ ዓላማውን “ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል” በተባለው መሠረት እንደሆነ ይናገራል፤ “የጥናት ሰነዱም” የተዘጋጀው ሕገ መንግሥቱን መሬት ላይ በማውረዱ ሒደት እንደሆነ ያትታል፡፡ ቢያንስ ጥናቱ፣ በአዲስ አበባ ማስፋፊያ ማስተር ፕላን ሳቢያ ተቆስቁሶ ለብዙ ንፁኃን ሕይወት ማለፍ መንስዔ የሆነውን በርካታ ጥያቄዎችን ያነገበው ሕዝባዊ አመፅ እንደምክንያት በመጥቀስ እውነት ለመናገር መድፈር ነበረበት፡፡ የዚህ ሰነድ ባለቤት ኦሕዴድ ቢሆንም የሕወሓትን ይሁንታ ሳያገኝ እዚህ ደረጃ እንደማይደርስ መገመት ቀላል ነው፡፡

‘ኢትዮጵያዊ ርስበርስ መባላቱን፥ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይችላልን?’

ትላንት      ነብይ ባገሩ አይከበርም ዛሬ      ነብይ ባገሩ አይኖርም ነገ      ነብይ ባገሩ አይፈጠርም (በዕውቀቱ ሥዩም) ፌስቡክ የትውልዳችን ማንነት ገመና ገላጭ ነው። የመግቢያዬ ግጥም ገጣሚ፣ በትውልድ ፈርጥነቱ ሊወደስ ሲገባው፥ የሚናገረውን እንኳ በማያውቅ መደዴ ሲዘለፍ መዋል የጀመረው ፌስቡክ ላይ ከወጣ ወዲህ ነው። ነገሩ የኛ ትውልድ፣ የፌስቡክ መንደር ድክመት ብቻ ነው ብዬ ባምንና ባልፈው ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን እንደጨጓራ ራሱን የበላው 'ያ ትውልድ'ም፣ የ'ያ ትውልድ' አሳዳጊም፣ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያው ሆኖ መሰለኝና ብዕሬን ለቁዘማ መዘዝኩ። አሁን ኢትዮጵያ 'ፈላስፋ' ነበራት ለማለት የምናጣቅሰው፣ ፈረንጆቹ "ኢትዮጵያዊ አይደለም" ሲሉ 'ዘራፍ' ብለን የምንሟገትለት ዘርዐ ያዕቆብ፣ በሐሳቡ ምክንያት ከትውልድ አገሩ አኵሱም ተሰዷል፣ ለማኝ ሆኖ ዋሻ ውስጥ ኖሯል፣ ጎንደር ዘልቆ ራሱን ቀይሮ ዕድሜውን ለመጨረስ ተገዷል። እርግጥ ነው ይህ መልካም ሰው የማሳደድ አባዜ የዓለም አባዜ ነበር። ይሁን እንጂ አባዜው ዛሬ ለቀሪው ዓለም 'ነበር' ሲሆን ለኛ ግን 'ነው' ሆኖ ዘልቋል። የግሪኩ ሶቅራጠስ፣ አፍላጦንን፣ አፍላጦን አሪስጣጣሊስን… እየተኩ ሲያልፉ የእኛዎቹ ዘርዐ ያዕቆብ እና ወራሹ ወልደ ሕይወት በወላድ አገር ምትክ አጥተው መካን ሆነው ቆመዋል። ከዓለም በከፋ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ሐሳብ ይዞ መምጣት በንጉሡም፣ በጳጳሱም፣ በምዕመኑም ያስቀጣል(ነበር)። ልዩነቱ ይኼ ነው። በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጊዜ ለንጉሥ አንሰግድም ያሉት አባ እስጢፋኖስ እና ደቂቆቻቸው ዕጣ ፈንታ መስዋዕትነት ነበር። በየዘመኑ የተለዩትን፣ የተሻሉትን ስንገድል ነው የኖር...

ESPDP: A New Loyal Ally to TPLF?

EPRDF is convinced that it has controlled the mood of public protests that had been escalating when State of Emergency (SoE) was declared. (Now, the directives are lifted up.) This is true especially for areas surrounding the Capital, Addis Ababa. People whom I talk to tend to forget the high tension back in September 2016.  After Christmas in 2016, new series of concerts recompensated their bankrupcy of cancelled concerts on the eve of Ethiopian new year; public festivals (such as Timkat) went on as quitely as in the old good days. Political oppositions are as divided as before; and, the superficial alliance against TPLF, that was observed among the divided dissenting elites during the heyday of protests, has crumbled at the wake of declaration of SoE decree. What so ever, post election 2005 changed EPRDF for good; so will post 2016 protests. In post 2005, the party declined in democratization records. It became a one-man party. Similarly, post 2016 protests are changing EP...

የፌሚኒዝም ሀሁ…

ፌሚኒዝምን በተመለከተ ሊያወዛግቡ የማይገባቸው ጥያቄዎች ሲያወዛግቡ እመለከታለሁ፡፡ ጥያቄዎቹን የማያነሷቸው ገና ውይይቱ ውስጥ ብዙም ያልቆዩ ሰዎች ናቸው እንዳልል አምናና ካቻምናም ይህንኑ ሲከራከሩ የነበሩ ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ በንባብ የበሰሉ ይመስላሉ፤ መጽሐፍ አሳትመው ፌሚኒዝምን ሊታገሉ የሞከሩም አልጠፉም፡፡ ስለዚህ እስኪ ምናልባት ‹በፌሚኒዝም ሀሁ› አልተግባባን እንደሆን በማለት ይህንን ጻፍኩ፣ ፌሚኒዝም ምንድን ነው? ፌሚኒዝም "ሴቶች ከወንዶች ዕኩል መብት እና ዕኩል ዕድል እንዲያገኙ የሚጥር ንቅናቄ" ነው፡፡ ፌሚኒስት ማለትም (ሴትም ትሁን ወንድ) የዓለማችን ስርዓተ ማኅበር አባታዊ (patriarchal ወይም ለወንዶች የሚያደላ ወይም የወንዶች የበላይነት ያለበት) መሆኑን በማመን፣ እንዲለወጥ በየዘርፉ ወይም በአኗኗር የተደራጀ ወይም ያልተደራጀ ጥረት  የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡ ፌሚኒዝም ብዙዎች አንደሚፈሩት አባታዊውን ስርዓት አፍርሶ በሴት የበላይነት የሚተካ ንቅናቄ አይደለም፡፡ እርግጥ ስር የሰደደው አባታዊው ስርዓተ ማኅበር በሴቶች የበላይነት ልተካህ ቢሉት እንኳን በቀላሉ እና በቅርብ ጊዜ የሚተካ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ፌሚኒዝም ሴቶችን ወንድ የማድረግ ንቅናቄም አይደለም፡፡ ዕኩልነት ሲባል - የመብት፣ የትምህርት እና የሥራ - እንጂ የቁመት፣ የጡንቻ እና የመሳሰሉት አይደለም፡፡ ፌሚኒዝም ሴቶች በራሳቸው እና በዓለማቸው ዕጣ ፈንታ ላይ መወሰን የሚስችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ፖለቲካዊ ዕድል ሁሉ ከወንዶች ጋር እንዲጋሩ ለማስቻል የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ እርግጥ ነው ሴቶች ዕኩል መብት እና ዕኩል ዕድል ማግኘታቸው መብቱን እና ዕድሉን የተቀማ/የተካፈሉት የሚመስለው ወንድ መኖሩ የሚገመት ነው፡፡ ትግሉ ብዙ ተጉ...

Who Builds Walls and Who Pays for Them?

The Great Wall of China was not built for its would-be historic value nor for the tourist attraction it earned now. Neither do other walls of the world such as the really ancient Sumerian's Amorite wall, the Walls of Constantinople, the Berlin Wall and many others including our own Harar City Wall. Who Builds Walls and Why? In contrary to the saying 'good fences make good neighbours', walls are evidences of distrust and hate. Sumerian's Amorite Wall was built 4,100 years ago by Sumerian rulers to keep Amorites out of Mesopotamia. Walls of Constantinople (today's Istanbul) were built in the 15th century by Byzantine empire to keep away Arab conquerors. Great Wall of China was built from the 3rd century BC to 17th century AD by the orders of kings to defend Ming dynasty and to keep northern nomadic tribes of Mongule out. Berlin wall was built in the 19th century to stop people escaping communist East Germany to the west. The difference here, it is not West...

How to Decrease Institutionalized Human Rights Violations in Ethiopia

Picture: Zeway Federal Prison /under construction/ Sometimes, I think we who criticize government for violating human rights don't know how to protect them ourselves. I think even if the regime changes, the violations may continue. History tells us institutions like Maekelawi continue to function as before regardless of regime changes. Sometimes, I also think, even if the government officials at the top don't want the rights violations, the individuals at the lower level may continue to violet them because there is no institutional way of holding them accountable. (Our cultural beliefs on physical punishment shouldn't be disregarded. Even mothers go to the extreme of steaming their  beloved children with pepper smoke when they think the latter made mistakes.)

ጉደኛውን ተራራ (Tullu Gudo) አየነው!

ዝዋይ ሐይቅ፣ በተለምዶ ዝዋይ በምትባለው ባቱ ከተማ ዳርቻ ላይ፣ በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 100 ማይሎች ርቆ የሚገኝ፣ 440 ስኵዌር ኪሎ ሜትር የሚሰፋ፣ ብዙም የማይወራለት፣ ብዙም ያልለማ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ፋይዳው የላቀ፣ ትልቅ ሐይቅ ነው። ሐይቁ 5 ደሴቶች አሉት። በደሴቶቹ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስር የሚተዳደሩ የተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች አሉ፤ የታቦታቱ ቁጥር 44 ነው ይባላል። በቱሉ ጉዶ ደሴት ላይ ባለችው የማርያም ቤተ ክርስትያን ጊቢ ውስጥ አንድ ሙዚዬም አለ። ሙዚዬሙ ውስጥ 'መጽሐፈ ሔኖክ' የሚባለው ዝነኛ መጽሐፍ አለ አሉ። ሔኖክ በመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች የኖህ ቅድመ አያት ነው ተብሎ ይታመናል። የአዳም ስድስተኛ የልጅ ልጁም ነው። ሔኖክ ከእግዜር ጋር በምድር ላይ ተንሸራሽሮ የጻፈው የጉዞ ማስታወሻ ነው 'መጽሐፈ ሔኖክ'። መጽሐፉ መጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ ውስጥ ባይካተትም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት በጣም ይከበራል። በዓለም ዙሪያም ታሪካዊ ፋይዳው ትልቅ ነው። የመጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፎች ከፊሎቹ 300 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ከፊሎቹ ደግሞ 100 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በኋላ የተዘጋጁ እንደሆነ በታሪክ ተመራማሪዎች ይታመናል። የመጽሐፈ ሔኖክ ታሪክ ሲወሳ መጀመሪያ (የኛ ከሆነው የግዕዙ መጽሐፍ በፊት) ፍልስጤም ውስጥ በእብራይስጥ እና በአርማይክ ቋንቋ ከተጻፈ በኋላ 800 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የገባበት ጠፍቶ ነበር። ከዛ ምንም እንኳ ከፊል የላቲን ትርጉሙ በአውሮጳ ቢኖርም፣ በ7ኛው ክፍለ ዘመን (ከ1,500 ዓመታት በኋላ) ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉው የግዕዝ ትርጉሙ መኖሩ ተሰማ። ከዛ በኋላ መጽሐፉን ለመስረቅ አውሮጳዎች ያልደከሙት የለም። ግን ሳይሳካ ቆይቷል። የፈረ...